እንኳን ደስ አላችሁየነባር 10 /90 እና 20/80 የኮንዶሚንየም ባለእድለኛ መሆን አለመሆኖን ስምዎትን አልያም የአመልካች መለያ ቁጥርዎን በመጠቀም አሁኑኑ በቀላሉ የሚያረጋግጡበት ነጻ የሆነ ድህረ ገጽ ሲሆን አጠቃቀሙም ቀላል ነው ::በቅርቡ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች የኮንዶሚንየም ቤት እጣ መውጣቱ ይተወቃል። ሆኖም ነዋሪዎችም እጣው እንደወጣላቸው ወይም እንዳልወጣላቸው የሚያረጋግጡበት ምቹ፣ ቀላልና ቀልጣፋ አማራጭ ድህረ ገጽ እንደሚያስፈል ተረድቼ ይህንን ድህረ ገጽ ለመስራት በቅቻለሁ ። ብዙዎችም በጉዳዩ ላይ ሀሳባቸውን እየሰነዘሩ ባሉበት በአሁኑ ጊዜ እኔም ችግሩን በመገንዘብ በቀላል መንገድ ህብረተሰቡ መረጃውን ብዙም ሳይቸገር እንዲያገኝ የሚያስችል ሶፍትዌር(Database system) በማዘጋጀት እንዲጠቀም እነሆ በረከት ብያለሁ። ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነው አገልግሎት ነዋሪው ስሙን በአማርኛ በመጻፍ ብቻ ወይም የአመልካች መለያ ቁጥሩን በማስገባት መረጃውን ማግኘት ያስችላል። በተለይም ለ 20/80 አሸናፊዎች በየተወዳደሩበት የቤት አይነት ተከፋፍሎ የተዘጋጀ በመሆኑ ያለብዙ ውጣ ውረድ መጠቀም ያስችላል::የራሶትንና የወዳጆችዎን የኮንዶሚንየም ቤት እጣ ባለእድለኛነት ለማወቅ ካሻዎ ይህን ድህረ ገጽ ይጠቀሙ ለሎችም እንዲጠቀሙ መረጃ ይስጡ። አጠቃቀም :ስማችሁ በተለያዩ የፊደል ዘሮች የሚጀምር ከሆነ ወይም በስማችሁ ውስጥየሚገኝ ከሆነ፡ ፊደሎቹን በመለዋወጥ እነድትሞክሩ እመክራለሁኝ:: ለምሳሌ: "ሀ ፣ ሐ፣ ሃ ፣ ኋ " የሚሉ ፊደላት በስማችሁ ካነ ፡ እንዲሁም " አ ፣ ዓ ፣ ዐ ፡ ፀ ፣ ጸ ፣ፃ ፣ ጻ፣ ሰ ፣ ሠ " በተለያየ አማራጭ መሞከር ያስፈልጋል::
For those of you who are the lucky one for this year's (2015) draw, I would like to say Congrats! and those of you who are not on this list please be patient that you will be on the next draw for sure. I am also wating for the next draw.
LOVE AND PEACE FOR ETHIOPIA FOREVER!!
Addis with construction of resident housesDocumentary :Condos in Addis |