ፍቅርና ሰላም ለኢትዮጵያ ለዘላለሙ!!

እንኳን ደስ አላችሁ

የነባር 10 /90 እና 20/80 የኮንዶሚንየም ባለእድለኛ መሆን አለመሆኖን ስምዎትን አልያም የአመልካች መለያ ቁጥርዎን በመጠቀም አሁኑኑ በቀላሉ የሚያረጋግጡበት ነጻ የሆነ ድህረ ገጽ ሲሆን አጠቃቀሙም ቀላል ነው ::

በቅርቡ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች የኮንዶሚንየም ቤት እጣ መውጣቱ ይተወቃል። ሆኖም ነዋሪዎችም እጣው እንደወጣላቸው ወይም እንዳልወጣላቸው የሚያረጋግጡበት ምቹ፣ ቀላልና ቀልጣፋ አማራጭ ድህረ ገጽ እንደሚያስፈል ተረድቼ ይህንን ድህረ ገጽ ለመስራት በቅቻለሁ ። ብዙዎችም በጉዳዩ ላይ ሀሳባቸውን እየሰነዘሩ ባሉበት በአሁኑ ጊዜ እኔም ችግሩን በመገንዘብ በቀላል መንገድ ህብረተሰቡ መረጃውን ብዙም ሳይቸገር እንዲያገኝ የሚያስችል ሶፍትዌር(Database system) በማዘጋጀት እንዲጠቀም እነሆ በረከት ብያለሁ። ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነው አገልግሎት ነዋሪው ስሙን በአማርኛ በመጻፍ ብቻ ወይም የአመልካች መለያ ቁጥሩን በማስገባት መረጃውን ማግኘት ያስችላል። በተለይም ለ 20/80 አሸናፊዎች በየተወዳደሩበት የቤት አይነት ተከፋፍሎ የተዘጋጀ በመሆኑ ያለብዙ ውጣ ውረድ መጠቀም ያስችላል::የራሶትንና የወዳጆችዎን የኮንዶሚንየም ቤት እጣ ባለእድለኛነት ለማወቅ ካሻዎ ይህን ድህረ ገጽ ይጠቀሙ ለሎችም እንዲጠቀሙ መረጃ ይስጡ።

ፍቅርና ሰላም ለኢትዮጵያ ለዘላለሙ!!

Tagel A.


አጠቃቀም  :

  • ስማችሁ በተለያዩ የፊደል ዘሮች የሚጀምር ከሆነ ወይም በስማችሁ ውስጥየሚገኝ ከሆነ፡ ፊደሎቹን በመለዋወጥ እነድትሞክሩ እመክራለሁኝ:: ለምሳሌ: "ሀ ፣ ሐ፣ ሃ ፣ ኋ " የሚሉ ፊደላት በስማችሁ ካነ ፡ እንዲሁም " አ ፣ ዓ ፣ ዐ ፡ ፀ ፣ ጸ ፣ፃ ፣ ጻ፣ ሰ ፣ ሠ " በተለያየ አማራጭ መሞከር ያስፈልጋል::

  • Power Geez 2009 ስትጠቀሙ ፊደላትን ደራርቦ የሚያሳይ ከሆነ "MICROSOFT WORD" ላይ በቅድሚያ በመጻፍ COPY በማድረግ "የ አመልካች ስም / የ አመልካች መለያ ቁጥር..." በሚለው ቦታ ላይ PASTE በማድረ SEARCH የሚለውን ይጫኑ::
  • Addis with construction of resident houses

    Documentary :Condos in Addis


    USING NAME OR ID , YOU CAN SEARCH HERE FOR 20 BY 80 STUDIO !

    Using the Application Id Number and Your First Name :